ደንገል ረግረግ በሌለበት ስፍራ ይበቅላልን? ቄጠማስ ውሃ በሌለበት ይለመልማልን?
እነሆ መልካቸው ያማረ፣ ሥጋቸው የወፈረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ይበሉ ጀመር።
እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፣ ከልቦናቸውም ቃልን የሚያወጡ አይደሉምን?
ገና በማደግ ላይ እያለ ሳይታጨድ፣ ከሌሎች ሣሮች ፈጥኖ ይደርቃል።
ከዚያ በላይ ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ ግን የደንገል ቅርጫት ወስዳ፣ በዝፍትና በቅጥራን ለቀለቀችው፤ ሕፃኑንም በውስጡ አስተኝታ ቅርጫቱን አባይ ወንዝ ዳር ቄጠማ መካከል አስቀመጠችው።