በተኛሁ ጊዜ ‘መቼ ነግቶ እነሣለሁ?’ እላለሁ፤ ሌሊቱ ይረዝማል፤ እስኪነጋም እገላበጣለሁ።
እነዚህ ሰዎች ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፤ ጨልሞም እያዩ፣ ‘ብርሃን ቀርቧል’ ይላሉ።
ደዌ በሌሊት ዐጥንቴን ይበሳል፤ የሚቈረጥመኝም ፋታ አይሰጠኝም።
እንደ ምሽት ጥላ ከእይታ ተሰውሬአለሁ፤ እንደ አንበጣም ረግፌአለሁ።
ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣ አዎን፤ ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣ ነፍሴ ጌታን ትጠባበቃለች።
ከመቃተቴ የተነሣ ዝያለሁ። ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ ዐልጋዬን አርሳለሁ፤ መኝታዬንም በእንባዬ አሾቃለሁ።
ዐይኖቼ እንዳይከደኑ ያዝሃቸው፤ መናገር እስኪሳነኝ ድረስ ታወክሁ።
“አንቺ የተጨነቅሽ ከተማ ሆይ፤ በዐውሎ ነፋስ የተናወጥሽ፣ ያልተጽናናሽም፤ እነሆ፤ በከበሩ ድንጋዮች አስጊጬ እገነባሻለሁ፤ በሰንፔር ድንጋይም እመሠርትሻለሁ።
ልብህ በፍርሀት ከመሞላቱና ዐይንህ ከሚያየው የተነሣ፣ ሲነጋ፣ “ምነው አሁን በመሸ!” ሲመሽ ደግሞ፣ “ምነው አሁን በነጋ!” ትላለህ።