ዐልጋዬ ያጽናናኛል፣ መኝታዬም ማጕረምረሜን ይቀንስልኛል ባልሁ ጊዜ፣
ሰላም የለኝም፤ ርጋታም የለኝም፤ ሁከት እንጂ ዕረፍት የለኝም።”
አንተ በሕልም ታስፈራራኛለህ፤ በራእይም ታስደነግጠኛለህ፤
ከመቃተቴ የተነሣ ዝያለሁ። ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ ዐልጋዬን አርሳለሁ፤ መኝታዬንም በእንባዬ አሾቃለሁ።
ዐይኖቼ እንዳይከደኑ ያዝሃቸው፤ መናገር እስኪሳነኝ ድረስ ታወክሁ።