የማይጣፍጥ ምግብ ያለ ጨው ይበላልን? ወይስ የዕንቍላል ውሃ ጣዕም አለውን?
ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚለይ፣ ጆሮ ቃላትን አይለይምን?
“ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ሰምቻለሁ፤ እናንተ ሁላችሁ የምታስጨንቁ አጽናኞች ናችሁ።
ምላስ ምግብን አጣጥሞ እንደሚለይ፣ ጆሮም የንግግርን ለዛ ለይቶ ያውቃል።
የቅንነት ቃል ምንኛ ኀያል ነው! የእናንተ ክርክር ግን ምን ፋይዳ አለው?
ክፋት በአንደበቴ አለን? አፌስ ተንኰልን መለየት አይችልምን?
የሜዳ አህያ ሣር እያለው፣ በሬስ ድርቆሽ እያለው፣ ይጮኻልን?
እንዲህ ዐይነቱን ምግብ እጸየፋለሁ፤ ለመንካትም አልፈልግም።
ቃልህ ለምላሴ ምንኛ ጣፋጭ ነው! ለአፌም ከማር ወለላ ይልቅ ጣዕም አለው።
የምታቀርበውን የእህል ቍርባን ሁሉ በጨው ቀምመው፤ የአምላክህ የቃል ኪዳን ጨው ከእህል ቍርባንህ አይታጣ፤ በቍርባንህም ላይ ጨው ጨምርበት።
“እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው ጣዕሙን ቢያጣ ጨውነቱን መልሶ ሊያገኝ ይችላልን? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ጥቅም አይኖረውም።
“ጨው መልካም ነው፤ ጨው ጣዕሙን ካጣ ግን እንዴት ተመልሶ ጣዕም ሊኖረው ይችላል?
ለእያንዳንዱ ሰው እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ በጨው እንደ ተቀመመ ሁልጊዜ በጸጋ የተሞላ ይሁን።