“አሁን ግን ፈቃዳችሁ ቢሆን ወደ እኔ ተመልከቱ፤ ፊት ለፊት እዋሻችኋለሁን?
በውኑ የአንተ መዘላበድ ሰውን ዝም ያሰኛልን? ስታፌዝስ የሚገሥጽህ የለም?
እናንተ ግን፣ በሐሰት የምትለብጡ ናችሁ፤ ሁላችሁ የማትረቡ ሐኪሞች ሆናችኋል።
“ይህ እንዲህ ካልሆነማ፣ የሚያስተባብለኝ ማን ነው? ቃሌን ከንቱ የሚያደርገውስ ማን ነው?”
ከንፈሬ ኀጢአትን አትናገርም፤ አንደበቴም ሽንገላ አይወጣውም።
ቃሌ ከቅን ልብ ይወጣል፤ ከንፈሬም የማውቀውን በትክክል ይናገራል።
ቃሌ ሐሰት እንዳልሆነ አረጋግጣለሁ፤ በዕውቀቱ ፍጹም የሆነ ሰው ከአንተ ጋራ ነው።