ሲራራ ነጋዴዎች ውሃ አጥተው መንገዳቸውን ይቀይራሉ፤ ወደ በረሓም ገብተው ይጠፋሉ።
በበጋ ወራት ግን ይጠፋል፤ በሙቀትም ጊዜ መፋሰሻው ላይ አይገኝም።
የቴማን ነጋዴዎች ውሃ ይፈልጋሉ፤ የሳባ መንገደኞችም ተስፋ ያደርጋሉ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ቅጣኝ፤ ብቻ በመጠኑ ይሁንልኝ፤ ፈጽሞ እንዳልጠፋ፣ በቍጣህ አትምጣብኝ።