ወንድሞቼ ግን እንደማያዛልቅ ጅረት፣ ለጊዜው ሞልቶ እንደሚፈስስ ወንዝ የማይታመኑ ናቸው፤
መከራህን ትረሳለህ፤ ዐልፎ እንደ ሄደ ጐርፍም ታስበዋለህ።
እናንተ ግን፣ በሐሰት የምትለብጡ ናችሁ፤ ሁላችሁ የማትረቡ ሐኪሞች ሆናችኋል።
ውሃ ከባሕር ውስጥ እንደሚያልቅ፣ የወንዝ ውሃም ጠፍቶ እንደሚደርቅ፣
“ወንድሞቼን ከእኔ አርቋል፤ ከሚያውቁኝም ተገለልሁ።
የቅርብ ወዳጆቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፤ የምወድዳቸውም በላዬ ተነሡ፤
በረዶ በሟሟ ጊዜ ወንዙ ይደፈርሳል፤ ዐመዳይም በቀለጠ ጊዜ ይሞላል፤
ከቍስሌ የተነሣ ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ሸሹኝ፤ ጎረቤቶቼም ርቀው ቆሙ።
እንጀራዬን የበላ፣ የምተማመንበትም የቅርብ ወዳጄ፣ ተረከዙን አነሣብኝ።
ወዳጄንና ባልንጀራዬን ከእኔ አራቅህ፤ ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ።
በመከራ ጊዜ በወስላታ ሰው መተማመን፣ በተበላሸ ጥርስና በሰለለ እግር እንደ መታመን ነው።
ወንድሞችህና የገዛ ቤተ ሰብህ፣ እነርሱ እንኳ አሢረውብሃል፣ በአንተም ላይ ይጮኻሉ፤ በመልካም ቢናገሩህም እንኳ አትመናቸው።
ሕመሜ ለምን ጸናብኝ? ቍስሌስ ለምን በረታብኝ? ለምንስ የማይፈወስ ሆነ? እንደሚያታልል ወንዝ፣ እንደሚያሳስት ምንጭ ትሆንብኛለህን?
ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤ ስለ አንተም ግድ የላቸውም። ጠላት እንደሚመታ መታሁህ፤ እንደ ጨካኝም ቀጣሁህ፤ በደልህ ታላቅ፣ ኀጢአትህም ብዙ ነውና።
በይሁዳ ቤተ መንግሥት የቀሩ ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎናውያን ባለሥልጣኖች ይወሰዳሉ፤ ሴቶቹም እንዲህ ይላሉ፤ “ ‘እነዚያ የተማመንህባቸው ወዳጆችህ፣ አሳሳቱህ፤ አሸነፉህ። እግርህ ጭቃ ውስጥ ተሰንቅሯል፤ ወዳጆችህ ጥለውህ ሄደዋል።’
“ስለ ሁላችሁ መናገሬ አይደለም፤ የመረጥኋቸውን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን፣ ‘እንጀራዬን የሚበላ ተረከዙን አነሣብኝ’ የሚለው የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው።
እነሆ፤ ሁላችሁም በየፊናችሁ የምትበታተኑበት ጊዜ ይመጣል፤ ያም ጊዜ አሁን ነው። እኔንም ብቻዬን ትተዉኛላችሁ፤ ይሁን እንጂ አባቴ ከእኔ ጋራ ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።
እነዚህ ሰዎች በፍቅር ግብዣችሁ ላይ ያለ አንዳች ኀፍረት ከእናንተ ጋራ ቀርበው የሚበሉ ነውረኞች ናቸው፤ ደግሞም ራሳቸውን ብቻ የሚመግቡ እረኞች ናቸው፤ እነርሱም በነፋስ የሚነዱ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች ናቸው፤ በመከር ወራት ፍሬ የማይገኝባቸው ከሥራቸው ተነቅለው ሁለት ጊዜ የሞቱ ዛፎች ናቸው።