የድንጋይ ጕልበት አለኝን? ሥጋዬስ ናስ ነውን?
“ኀይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው! ደካማውንስ ምንኛ አዳንኸው!
ዐጥንቱ እንደ ናስ ቱቦ፣ እጅና እግሮቹም እንደ ብረት ዘንግ ናቸው።
ደረቱ እንደ ዐለት የጠጠረ፣ እንደ ወፍጮ ድንጋይም የጠነከረ ነው።
“አሁንም ተስፋ አደርግ ዘንድ ብርታቴ፣ እታገሥስ ዘንድ አለኝታዬ ምንድን ነው?
ያልተሳካልኝ ሰው ነኝና፣ ራሴን ለመርዳት ምን ጕልበት አለኝ?