ኢዮብም በዚህ ሁኔታ አርጅቶ፣ ዕድሜ ጠግቦ ሞተ።
አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ፤ ዕድሜም ጠግበህ ወደ መቃብር ትወርዳለህ፤
ከዚያም ዐረፈ፤ ዕድሜ ጠግቦ በመልካም ሽምግልና ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።
ከዚህ በኋላ ኢዮብ አንድ መቶ አርባ ዓመት ኖረ፤ ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ።
የእህል ነዶ ጐምርቶ በወቅቱ እንደሚሰበሰብ፣ ዕድሜ ጠግበህ ወደ መቃብር ትሄዳለህ።
ረዥም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።”
በቀኝ እጇ ረዥም ዕድሜ አለ፤ በግራ እጇም ሀብትና ክብር ይዛለች።
ይኸውም፣ የምሰጣችሁን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ሁሉ በመጠበቅ፣ ዕድሜያችሁ እንዲረዝም፣ አንተ፣ ልጆችህና ከእነርሱ በኋላ የሚመጡት ልጆቻቸው በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትፈሩት ዘንድ ነው።