እንደ ወፍ አልምደኸው ከርሱ ጋራ ልትጫወት ትችላለህ? ወይስ ለሴት አገልጋዮችህ መጫወቻነት ታስረዋለህን?
የወንዞችን ምንጭ ይበረብራል፤ የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል።
እንዲያርስልህ ልትጠምደው ትችላለህ? ወይስ እየተከተለህ ዕርሻህን ይጐለጕልልሃልን?
ለዘላለም ባሪያ ታደርገው ዘንድ፣ ከአንተ ጋራ ይዋዋላልን?
ነጋዴዎችስ በርሱ ላይ ይከራከራሉን? ለቸርቻሪዎችስ ያከፋፍሉታል?