የሆዱ ሥር እንደ ሸካራ ገል ነው፤ እንደ መውቂያ መሣሪያም በጭቃ ላይ ምልክት ጥሎ ያልፋል።
ቈመጥ በርሱ ፊት እንደ ገለባ ነው፤ ጦር ሲሰበቅ ይሥቃል።
እንደሚፈላ ምንቸት ጥልቁን ያናውጠዋል፤ ባሕሩንም እንደ ሽቱ ብልቃጥ ያደርገዋል።
“እነሆ፣ አዲስ የተሳለና ባለጥርስ ማሄጃ አደርግሃለሁ፤ ተራሮችን ታሄዳለህ፤ ታደቅቃቸዋለህ፤ ኰረብቶችንም ገለባ ታደርጋቸዋለህ።