እርሱ ብረትን እንደ አገዳ፣ ናስንም እንደ ነቀዘ ዕንጨት ይቈጥራል።
ጦር፣ ፍላጻ ወይም ዐንካሴ፣ ሰይፍም ቢያገኘው አንዳች አይጐዳውም።
ቀስት አያባርረውም፤ የወንጭፍ ድንጋይም ለርሱ እንደ ገለባ ነው።