እርሱ በተነሣ ጊዜ፣ ኀያላን ይርዳሉ፤ በሚንቀሳቀስበትም ጊዜ ወደ ኋላ ያፈገፍጋሉ።
ሌዋታንን ለማነሣሣት የተዘጋጁ፤ ቀንንም የሚረግሙ ያን ቀን ይርገሙት።
ደረቱ እንደ ዐለት የጠጠረ፣ እንደ ወፍጮ ድንጋይም የጠነከረ ነው።
ጦር፣ ፍላጻ ወይም ዐንካሴ፣ ሰይፍም ቢያገኘው አንዳች አይጐዳውም።
በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው።