በሸንበቆ ማገዶ ላይ ከተጣደ ድስት እንደሚወጣ እንፋሎት፣ ከአፍንጫው ጢስ ይትጐለጐላል።
እንደ አንበጣ የምታስዘልለው አንተ ነህን? የማንኰራፋቱም ገናናነት አስፈሪ ነው።
ከአፉ ፍም ይወጣል፤ የእሳት ትንታግ ይረጫል።
እስትንፋሱ ከሰል ያቀጣጥላል፤ የእሳትም ነበልባል ከአፉ ይወጣል።