እንጥሽታው የብርሃን ብልጭታ ያወጣል፤ ዐይኖቹም እንደ ማለዳ ጮራ ናቸው።
አጥቢያ ኮከቦቹ ይጨልሙ፤ ብርሃንን እየጠበቀ ይጣ፤ የንጋት ጮራ ሲፈነጥቅ አይይ።
እርስ በርስ የተገጣጠሙ ናቸው፤ አንዱ ከአንዱ ጋራ ተጣብቋልና ማንም ሊለያያቸው አይችልም።
ከአፉ ፍም ይወጣል፤ የእሳት ትንታግ ይረጫል።
ራሱና ጠጕሩም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር፣ እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፤ ዐይኖቹም የእሳት ነበልባል ይመስሉ ነበር።