እኔ እንዳየሁ ክፋትን የሚያርሱ፣ መከራንም የሚዘሩ ያንኑ ያጭዳሉ።
በዐጸፋው አንዳች አያገኝምና፤ ከንቱን ነገር በመታመን ራሱን አያታልል።
መከራን ይፀንሳሉ፤ ክፋትንም ይወልዳሉ፤ በሆዳቸውም ተንኰል ይጠነስሳሉ።”
የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፤ የዕቅዳቸውንም ውጤት ይጠግባሉ።
ክፋትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፤ የቍጣውም በትር ይጠፋል።
በተከልህበት ቀን እንዲበቅል፣ በዘራህበትም ማግስት እንዲያብብ ብታደርግ እንኳ፣ መከሩ በደዌና በማይሽር ሕመም ቀን፣ እንዳልነበረ ይሆናል።
“የገዛ መንገድሽና ተግባርሽ፣ ይህን አምጥቶብሻል፤ ይህም ቅጣትሽ ነው፤ ምንኛ ይመርራል! እንዴትስ ልብ ይሰብራል!”
“ነፋስን ይዘራሉ፤ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤ አገዳው ዛላ የለውም፤ ዱቄትም አይገኝበትም፤ እህል አፍርቶ ቢገኝም፣ ባዕዳን ይበሉታል።
ይህን አስታውሱ፤ ጥቂት የዘራ ጥቂት ያጭዳል፤ ብዙ የዘራ ብዙ ያጭዳል።