ያለ ጥበብ ይሞቱ ዘንድ፣ የድንኳናቸው ገመድ አልተነቀለምን?’
በርግጥ የክፉ ሰው መኖሪያ፣ እግዚአብሔርንም የማያውቅ ሰው መድረሻ ይህ ነው።”
ጠቢባን የሚሆኑት በዕድሜ የገፉ ብቻ አይደሉም፤ የሚያስተውሉም ሽማግሌዎች ብቻ አይደሉም።
ባይሰሙ ግን፣ በሰይፍ ይጠፋሉ፤ ያለ ዕውቀትም ይሞታሉ።
ጠላቶችህ ኀፍረት ይለብሳሉ፤ የክፉዎችም ድንኳን ይጠፋል።”
ሰዎችን ስለ ኀጢአታቸው ለመቅጣት ትገሥጻቸዋለህ፤ ሀብታቸውንም ብል እንደ በላው ታደርጋለህ፤ በርግጥ ሰው ሁሉ ተን ብቻ ነው። ሴላ
እነሆ፤ ዘመኔን በስንዝር ለክተህ አስቀመጥህ፤ ዕድሜዬም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው፤ በርግጥ የሰው ሁሉ ሕይወት ተን ነው። ሴላ
እንደ በጎች ለሲኦል የተዳረጉ ናቸው፤ ሞትም እረኛቸው ይሆናል፤ ቅኖች በማለዳ ይገዟቸዋል፤ አካላቸው ከክብር ቤታቸው ርቆ፣ በሲኦል ይፈራርሳል።
ሰው በሀብቱ እንደ ተከበረ አይዘልቅም፤ ታይተው የሚጠፉ እንስሳትን ይመስላል።
ከተግሣጽ ጕድለት የተነሣ ይሞታል፤ ከቂልነቱ ብዛት መንገድ ይስታል።
የሚያዩህም አትኵረው እየተመለከቱህ፣ በመገረም ስለ አንተ እንዲህ ይላሉ፤ “ያ ምድርን ያናወጠ፣ መንግሥታትን ያንቀጠቀጠ፣ ይህ ሰው ነውን?
እስትንፋስ አፍንጫው ላይ ባለች በሰው አትታመኑ፤ ከቶ ምን የሚበጅ ነገር አለው!
“እግዚአብሔር ግን፣ ‘አንተ ሞኝ፤ ነፍስህን በዚህች ሌሊት ከአንተ ሊወስዱ ይፈልጓታል፤ እንግዲህ፣ ለራስህ ያከማቸኸው ለማን ይሆናል?’ አለው።
ፀሓይ በነዲድ ሙቀቷ ወጥታ ሣሩን ታጠወልጋለችና፤ አበባው ይረግፋል፤ ውበቱም ይጠፋል፤ እንዲሁም ባለጠጋ ሰው፣ በዕለት ተግባሩ ሲዋትት ሳለ ይጠፋል።