በገደል ላይ ይኖራል፤ በዚያም ያድራል፤ ምሽጉም የቋጥኝ ጫፍ ነው።
ንስር ወደ ላይ የሚመጥቀው፣ ጐጆውንም በከፍታ ላይ የሚሠራው፣ በአንተ ትእዛዝ ነውን?
እዚያ ሆኖ የሚነጥቀውን ይቃኛል፤ ዐይኑም ከሩቅ አጥርቶ ያያል።
ዮናታን ወደ ፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር ለመሻገር በፈለገበት መተላለፊያ ግራና ቀኝ አንዱ ቦጼጽ ሌላው ሴኔ የተባሉ ሁለት ሾጣጣ ዐለቶች ነበሩ።