ከሚብረቀረቀው ጦርና ዐንካሴ ጋራ፣ የፍላጻው ኰረጆ ጐኑ ላይ ይንኳኳል።
ያለ አንዳች ሥጋት፣ በፍርሀት ላይ ይሥቃል፤ ሰይፍ ቢመዘዝበትም ወደ ኋላ አይልም።
በወኔ መሬቱን እየጐደፈረ ወደ ፊት ይሸመጥጣል፤ የመለከት ድምፅ ሲሰማ ያቅበጠብጠዋል።
የወታደሮቹ ጋሻ ቀይ ነው፤ ተዋጊዎቹ ቀይ ልብስ ለብሰዋል፤ ዝግጁ በሆኑበት ቀን፣ የሠረገሎቹ ብረት ያብረቀርቃል፤ የጦሩ ዘንግ ይወዛወዛል።