እንደ አንበጣ የምታስዘልለው አንተ ነህን? የማንኰራፋቱም ገናናነት አስፈሪ ነው።
“ለፈረስ ጕልበትን ትሰጠዋለህን? ዐንገቱንስ ጋማ ታለብሰዋለህን?
እንደ ምሽት ጥላ ከእይታ ተሰውሬአለሁ፤ እንደ አንበጣም ረግፌአለሁ።
የጠላት ፈረሶች ፉርፉርታ፣ ከዳን ይሰማል፤ በድንጉላ ፈረሶቻቸው ማሽካካት፣ መላዋ ምድር ተንቀጠቀጠች። ምድሪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ ከተማዪቱንና በውስጧ የሚኖሩትን ሁሉ፣ ሊውጡ መጡ።
ገለባ እንደሚበላ እንደሚንጣጣ እሳት፣ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ኀያል ሰራዊት፣ የሠረገሎችን ድምፅ የሚመስል ድምፅ እያሰሙ፣ በተራሮች ጫፍ ላይ ይዘልላሉ።