Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ኢዮብ 39:10

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲያርስልህ ልትጠምደው ትችላለህ? ወይስ እየተከተለህ ዕርሻህን ይጐለጕልልሃልን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መልእክተኛም ወደ ኢዮብ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “በሬዎች እያረሱ፣ አህዮችም በአጠገባቸው እየጋጡ ሳሉ፣

ጕልበቱ ብርቱ ስለ ሆነ ትተማመንበታለህ? ከባዱን ሥራህንስ ለርሱ ትተዋለህ?

“ለሜዳ አህያ ነጻነት የሰጠው ማን ነው? እስራቱንስ ማን ፈታለት?

በከተማ ውካታ ይሥቃል፤ የነጂውንም ጩኸት አይሰማም።

“ጐሽ ያገለግልህ ዘንድ ይታዘዛልን? በበረትህስ አጠገብ ያድራልን?

እንደ ወፍ አልምደኸው ከርሱ ጋራ ልትጫወት ትችላለህ? ወይስ ለሴት አገልጋዮችህ መጫወቻነት ታስረዋለህን?

ዐራሾች ጀርባዬን ዐረሱት፤ ትልማቸውንም አስረዘሙት።”

እናንተ በለኪሶ የምትኖሩ፣ ፈረሶችን ከሠረገላው ጋራ አያይዙ፤ ለጽዮን ሴት ልጅ፣ የኀጢአት መጀመሪያ እናንተ ነበራችሁ፤ የእስራኤል በደል በእናንተ ዘንድ ተገኝቷልና።

እግዚአብሔር ከግብጽ አወጣቸው፤ ብርታታቸውም እንደ ጐሽ ብርታት ነው።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች