ባድማውንና በረሓውን መሬት የሚያጠግብ፣ ሣርም እንዲበቅልበት የሚያደርግ ማን ነው?
ሰዎችን ለመቅጣት ደመና ያመጣል፤ ወይም በዚሁ ምድሩን አጠጥቶ ፍቅሩን ይገልጻል።
ከላይ ከእልፍኝህ ተራሮችህን ታጠጣለህ፤ ምድርም በሥራህ ፍሬ ትረካለች።
ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ፣ ለእንስሳት ሣርን፣ ለሰው ልጆች ሥራ ዕፀዋትን ታበቅላለህ፤
ምድረ በዳውን ወደ ውሃ መከማቻ፣ ደረቁንም ምድር ወደ ውሃ ምንጭ ቀየረ።
ሰማይን በደመናት የሚሸፍን እርሱ ነው፤ ለምድርም ዝናብን ይሰጣል፤ በተራሮችም ላይ ሣር ያበቅላል።
የምድረ በዳው ሣር እጅግ ለመለመ፤ ኰረብቶችም ደስታን ተጐናጸፉ።