ይኸውም ለመከራ ጊዜ፣ ለጦርነትና ለውጊያ ቀን ያስቀመጥሁት ነው።
“ልባቸው ከእግዚአብሔር የራቀ፣ ቍጣን ያስተናግዳሉ፤ በሰንሰለት ባሰራቸውም ጊዜ እንኳ ወደ እርሱ አይጮኹም።
እርሱ ሕዝብን የሚያስተዳድረው፣ ምግብንም አትረፍርፎ የሚሰጣቸው በዚህ መንገድ ነው።
“ወደ በረዶው መጋዘን ገብተሃልን? የዐመዳዩንስ ማከማቻ አይተሃልን?
መብረቅ ወደሚሠራጭበት ቦታ የሚያደርሰው መንገድ፣ የምሥራቅም ነፋስ በምድር ላይ ወደሚበተንበት ስፍራ የሚወስደው የትኛው ነው?
ስለዚህ ነገ በዚህ ጊዜ ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በግብጽ ላይ ወርዶ የማያውቅ አስከፊ የበረዶ ማዕበል እልካለሁ።
በረዶ ወረደ፤ መብረቅም አብረቀረቀ፤ ግብጽ አገር ከሆነችበት ዘመን አንሥቶ በምድሪቱ ሁሉ እንደዚህ ያለ አስከፊ ማዕበል ሆኖ አያውቅም።
እግዚአብሔር በሚነድድ ቍጣና በሚባላ እሳት፣ በወጀብና በነጐድጓድ፣ በበረዶም ድንጋይ፣ ግርማ የተሞላበትን ድምፁን ሰዎች እንዲሰሙ አድርጎ ያሰማል፤ ክንዱም ስትወርድ ያሳያቸዋል።
ዶፍ ወረደ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያን ቤት መታው፤ ቤቱም ወደቀ፤ አወዳደቁም የከፋ ነበር።”
ከቤትሖሮን ወደ ዓዜቃ ቍልቍል በሚወስደው መንገድ ላይ፣ ከእስራኤላውያን ፊት በሚሸሹበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሰማይ ትልልቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸው፤ በእስራኤላውያን ሰይፍ ካለቁት ይልቅ በወረደው የበረዶ ድንጋይ ያለቁት በልጠው ተገኙ።
በሚዛን ሲመዘን እያንዳንዱ አርባ ዐምስት ኪሎ ግራም የሚሆን ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ መቅሠፍቱ እጅግ አሠቃቂ ስለ ነበር፣ ሰዎቹ ከበረዶው መቅሠፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ።