እንስሳት ይጠለላሉ፤ በየዋሻቸውም ይቈያሉ።
እነርሱ በዋሻ ውስጥ ያደባሉ፤ በደን ውስጥም ይጋደማሉ።
የአንበሳ ግልገሎች ምግብ ፍለጋ ይጮኻሉ፤ የሚበሉትንም ከእግዚአብሔር ይሻሉ።
ፀሓይ በወጣች ጊዜም ይመለሳሉ፤ በየጐሬያቸውም ገብተው ይተኛሉ።