እጆቹን በመብረቅ ይሞላቸዋል፤ ዒላማውንም እንዲመታ ያዝዘዋል።
ደመናዎቹን በላዩ ዘርግቶ፣ የሙሉውን ጨረቃ ፊት ይጋርዳል።
ደመናትን ርጥበት ያሸክማቸዋል፤ መብረቁንም በውስጣቸው ይበትናል።
ያዘዘውን ለመፈጸም፣ እርሱ በሚሰጠው መመሪያ፣ በመላው የምድር ገጽ ላይ ይሽከረከራሉ።
እግዚአብሔር ደመናትን እንዴት እንደሚቈጣጠር፣ መብረቁንም እንዴት እንደሚያባርቅ ታውቃለህን?
መብረቆችን መስደድ ትችላለህ? እነርሱስ፣ ‘እነሆ፤ እዚህ አለን’ ይሉሃል?
እርሱ ደመናትን ከምድር ዳርቻ ያስነሣል፤ መብረቅ ከዝናብ ጋራ እንዲወርድ ያደርጋል፤ ነፋሳትንም ከማከማቻው ያወጣል።
እሳትና በረዶ፣ ዐመዳይና ጭጋግ፣ ትእዛዙንም የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስ፣
ጨለማን መሰወሪያው፣ በዙሪያውም አጐበሩ አደረገው፤ በዝናብ ዐዘል ጥቍር ደመናም ተሸፈነ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከተግሣጽህ የተነሣ፣ ከአፍንጫህም እስትንፋስ የተነሣ፣ የባሕር ወለል ታየ፤ የምድር መሠረቶችም ተገለጡ።
ብዙ ቀን፣ ፀሓይንም ከዋክብትንም ማየት ስላልተቻለና ነፋስ ስለ በረታብን፣ ለመትረፍ የነበረን ተስፋ ሁሉ ተሟጠጠ።