ደመናት ጠል ያንጠባጥባሉ፤ ዶፍም በሰው ላይ ይወርዳል።
“የውሃን ነጠብጣብ ወደ ላይ ያተንናል፤ መልሶም በዝናብ መልክ በጅረቶች ላይ ያወርዳል፤
ደመናትን እንዴት እንደሚዘረጋ፣ ከድንኳኑም እንዴት እንደሚያንጐደጕድ ሊረዳ የሚችል ማን ነው?
ዝናብ አባት አለውን? የጤዛን ጠብታ ማን ወለደው?
“ድምፅህን ወደ ደመናት አንሥተህ፣ ራስህን በጐርፍ ማጥለቅለቅ ትችላለህን?
ለዘመኑ በጎነትህን ታጐናጽፈዋለህ፤ ሠረገላህም በረከትን ተሞልቶ ይፈስሳል።
በዕውቀቱ ቀላያት ተከፈሉ፤ ደመናትም ጠልን አንጠበጠቡ።