“ለአንተና ዐብረውህ ላሉት ባልንጀሮችህ፣ መልስ መስጠት እፈልጋለሁ።
ከክፉ አድራጊዎች ጋራ ይተባበራል፤ ከኀጢአተኞችም ጋራ ግንባር ይፈጥራል።
ደግሞ ‘ያገኘሁት ጥቅም ምንድን ነው? ኀጢአት ባለመሥራቴስ ምን አተረፍሁ?’ ብለህ ጠይቀኸዋል።
ቀና ብለህ ወደ ሰማይ እይ፤ ከአንተ በላይ ከፍ ብለው ያሉትንም ደመናት ተመልከት።
ከጠቢብ ጋራ የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ የሞኝ ባልንጀራ ግን ጕዳት ያገኘዋል።