“አስተዋዮች ይናገራሉ፤ የሚሰሙኝም ጠቢባን እንዲህ ይሉኛል፤
“ስለዚህ፣ እናንተ አስተዋዮች ስሙኝ፤ ክፋትን ማድረግ ከእግዚአብሔር ዘንድ፣ በደልንም መፈጸም ሁሉን ቻይ አምላክ ይራቅ።
“ማስተዋል ካለህ ይህን ስማ፤ እኔ የምለውንም አድምጥ።
“እናንተ ጠቢባን፣ ቃሌን ስሙ፤ ዐዋቂዎችም አድምጡኝ።
ታዲያ አንተ ለመናዘዝ ፈቃደኛ ሳትሆን፤ እግዚአብሔር እንደ ወደድህ ይከፍልሃልን? መወሰን ያለብህ አንተ ነህ እንጂ፣ እኔ አይደለሁም፤ እንግዲህ የምታውቀውን ንገረኝ።
‘ኢዮብ ያለ ዕውቀት ይናገራል፤ ቃሉም ማስተዋል ይጐድለዋል።’
የሚበጀንን እንምረጥ፣ መልካሙንም ዐብረን እንወቅ።
ይህን የምናገረው አስተዋይ ለሆኑ ሰዎች ነው፤ ስለምናገረው ነገር እናንተው ፍረዱ።