ምላስ ምግብን አጣጥሞ እንደሚለይ፣ ጆሮም የንግግርን ለዛ ለይቶ ያውቃል።
ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚለይ፣ ጆሮ ቃላትን አይለይምን?
እኔ ግን በነፍሱ ላይ ክፉ እንዲመጣ በመራገም፣ አንደበቴን ለኀጢአት ከቶ አሳልፌ አልሰጠሁም።
እንግዲህ አፌን እከፍታለሁ፤ አንደበቴም ይናገራል።
“እናንተ ጠቢባን፣ ቃሌን ስሙ፤ ዐዋቂዎችም አድምጡኝ።
የሚበጀንን እንምረጥ፣ መልካሙንም ዐብረን እንወቅ።
ክፋት በአንደበቴ አለን? አፌስ ተንኰልን መለየት አይችልምን?
መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉንም ነገር ይመረምራል፤ ራሱ ግን በማንም አይመረመርም።
ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙን ከክፉው ለመለየት ራሳቸውን ላስለመዱ፣ ለበሰሉ ሰዎች ነው።