“ማስተዋል ካለህ ይህን ስማ፤ እኔ የምለውንም አድምጥ።
ነገር ግን እኔም እንደ እናንተ አእምሮ አለኝ፤ ከእናንተ አላንስም፤ እንዲህ ያለውን ነገር የማያውቅ ማን ነው?
ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት በጠፋ፣ ሰውም ወደ ዐፈር በተመለሰ ነበር።
ፍትሕን የሚጠላ ሊያስተዳድር ይችላልን? አንተስ ጻድቁንና ኀያል የሆነውን ትኰንናለህ?