በእውነት እግዚአብሔር ክፋትን አይሠራም፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ፍትሕን አያጣምምም።
እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ በቅን አይፈርድምን?”
“ስለዚህ፣ እናንተ አስተዋዮች ስሙኝ፤ ክፋትን ማድረግ ከእግዚአብሔር ዘንድ፣ በደልንም መፈጸም ሁሉን ቻይ አምላክ ይራቅ።
እርሱን መንገድ የሚመራው፣ ወይም ‘ይህን አጥፍተሃል’ የሚለው ማን ነው?
እግዚአብሔር ፍትሕን ያጣምማልን? ሁሉን ቻይ አምላክስ ጽድቅን ያጣምማልን?
እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፤ የጽድቅ ሥራም ይወድዳል፤ ቅኖችም ፊቱን ያያሉ።
እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ፣ በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።