የምትለው ካለህ፣ መልስ ስጠኝ፤ ትክክለኛነትህንም ማወቅ እፈልጋለሁና ተናገር፤
“እነሆ፣ ምክራችሁን፣ በእኔ ላይ ያሤራችሁትንም ተረድቻለሁ።
እናንተን እንደ ቅኖች መቍጠር፣ የማላደርገው ነገር ነው፤ ጨዋነቴንም እስክሞት ድረስ አልጥልም።
“ኢዮብ ሆይ፤ ልብ ብለህ ስማኝ፤ እኔ ልናገር፤ አንተ ዝም በል።
አለዚያ፣ ዝም ብለህ ስማኝ፤ እኔም ጥበብን አስተምርሃለሁ።”
የምትችል ከሆነ መልስልኝ፤ ተዘጋጅተህም በፊቴ ቁም።