እንዳልነበረ ሆኖ ሥጋው ይመነምናል፤ ተሸፍኖ የነበረው ዐጥንቱም ገጥጦ ይወጣል።
“እንደ በሰበሰ ግንድ፣ ብል እንደ በላው ልብስ፣ ሕይወት እያደር ማለቅ ነው።
አንድ ጊዜ ፈጽመህ ትበረታለህ፤ እርሱም ያልፋል፤ ገጽታውን ትቀይራለህ፤ ትሸኘዋለህም።
የገዛ አካሉ ሕመም ብቻ ይሰማዋል፤ ለራሱም ብቻ ያለቅሳል።”
ጭምትርትር ያደረግኸኝ ምስክር ሆኖብኛል፣ ዐጥንቴን ያወጣው ክሳቴም ያጋልጠኛል።
ቈዳና ዐጥንት ብቻ ሆኜ ቀረሁ፤ ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።
አካሌ ቈስሎ ትልና ቅርፊት ለብሷል፤ ቈዳዬ አፈክፍኳል፤ ቍስሌም አመርቅዟል።
ሰዎችን ስለ ኀጢአታቸው ለመቅጣት ትገሥጻቸዋለህ፤ ሀብታቸውንም ብል እንደ በላው ታደርጋለህ፤ በርግጥ ሰው ሁሉ ተን ብቻ ነው። ሴላ
በዕድሜህ መጨረሻ ታቃሥታለህ፤ ሥጋህና ሰውነትህ ሲከዳህ።