ኢዮብ ግን ቃሉን በእኔ ላይ አልሰነዘረም፤ እኔም እንደ እናንተ አነጋገር መልስ አልሰጠውም።
‘እኛ ጥበብ አግኝተናል፤ ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ይርታው’ አትበሉ።
“እነርሱ ተስፋ ቈርጠው የሚሉት የላቸውም፤ የሚናገሩትም ጠፍቷቸዋል።
የምትችል ከሆነ መልስልኝ፤ ተዘጋጅተህም በፊቴ ቁም።