“አሁን ግን ልጆቻቸው በዘፈን ይሣለቁብኛል፤ በእነርሱም ዘንድ መተረቻ ሆኛለሁ።
“እግዚአብሔርን ጠርቼ የመለሰልኝ ሰው ብሆንም፣ ለባልንጀሮቼ መሣቂያ ሆኛለሁ፤ ጻድቅና ያለ ነቀፋ ሆኜ እያለሁ፣ መሣቂያ ሆኛለሁ።
“አምላክ ለሰው ሁሉ መተረቻ፣ ፊቱ ላይ የሚተፋበት ሰውም አደረገኝ።
ስማቸው የማይታወቅ ሞኞች ናቸው፤ ከምድሪቱም ተባርረዋል።
በሕዝቦች ዘንድ መተረቻ፣ በሰዎች መካከል በንቀት ራስ መነቅነቂያ አደረግኸን።
እግዚአብሔር ሆይ፤ አታለልኸኝ፤ እኔም ተታለልሁ፤ አንተ ከእኔ እጅግ በረታህ፤ አሸነፍህም፤ ቀኑን ሙሉ ማላገጫ ሆንሁ፤ ሁሉም ተዘባበቱብኝ።
ለሕዝቤ ሁሉ ማላገጫ ሆንሁኝ፤ ቀኑን ሙሉ በመሣለቅ ያዜሙብኛል።
“ጠላቶቻችን ሁሉ፣ አፋቸውን በእኛ ላይ ከፈቱ።
ተመልከታቸው! ቆመውም ሆነ ተቀምጠው፣ በዘፈናቸው ይሣለቁብኛል።