በጫካ ውስጥ ያናፋሉ፤ በእሾኻማ ቍጥቋጦ መካከልም ይታፈጋሉ።
እርሱም እንደ ዱር አህያ ይሆናል፤ እጁንም ባገኘው ሰው ሁሉ ላይ ያነሣል፤ ያገኘውም ሁሉ እጁን ያነሣበታል፤ ከወንድሞቹ ሁሉ ጋራ እንደ ተጣላ ይኖራል።”
ጅል ሰው ጥበበኛ ከሚሆን ይልቅ፣ የሜዳ አህያ ሰው ሆኖ ቢወለድ ይቀላል።
በዐለት መካከል በምድር ጕድጓድ፣ በደረቅ ሸለቆ ዋሻ ውስጥ ለመኖር ተገደዱ።
ስማቸው የማይታወቅ ሞኞች ናቸው፤ ከምድሪቱም ተባርረዋል።
የሜዳ አህያ ሣር እያለው፣ በሬስ ድርቆሽ እያለው፣ ይጮኻልን?
በያለበት እሾኽ በቅሎበታል፤ መሬቱም ዐረም ለብሷል፤ ቅጥሩም ፈራርሷል።