በቀኜ በኩል ባለጌዎች ሆ! ብለው ተነሡብኝ፤ ለእግሬም ወጥመድ ዘረጉ፤ የዐፈር ድልድልም አዘጋጁብኝ።
ሰዎች በፌዝ አፋቸውን ከፈቱብኝ፤ በንቀት ጕንጬን ጠፈጠፉኝ፤ በአንድነትም በላዬ ተሰበሰቡ።
ሰራዊቱ ገፍተው መጡ፤ በዙሪያዬ ምሽግ ሠሩ፤ ድንኳኔንም ከብበው ሰፈሩ።
ሕፃናት እንኳ ይንቁኛል፤ ባዩኝም ቍጥር ያላግጡብኛል።
ሕዝብ እርስ በርሱ ይጨቋቈናል፤ ሰው በሰው ላይ፤ ባልንጀራ በባልንጀራው ላይ፣ ወጣቱ በሽማግሌው ላይ፣ ተራው ሰው በተከበረው ላይ ይነሣል።