ያ ሌሊት በድቅድቅ ጨለማ ይያዝ፤ ከዓመቱ ቀናት ጋራ አይቈጠር፤ ከወራቱ በአንዱም ውስጥ አይግባ።
ጨለማና የሞት ጥላ ይውረሱት፤ ደመናም በላዩ ላይ ይረፍ፤ ብርሃኑን ጽልመት ይዋጠው።
ያ ሌሊት መካን ይሁን፤ እልልታም አይሰማበት።