ያ ቀን ጨለማ ይሁን፤ እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው፤ ብርሃንም አይብራበት።
“የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፤ ‘ወንድ ልጅ ተፀነሰ’ የተባለበት ሌሊት።
ጨለማና የሞት ጥላ ይውረሱት፤ ደመናም በላዩ ላይ ይረፍ፤ ብርሃኑን ጽልመት ይዋጠው።
ይህም የጨለማና የጭጋግ ቀን፣ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው። የንጋት ብርሃን በተራሮች ላይ እንደሚወጣ፣ ኀያልና ብዙ ሰራዊት ይመጣል፤ ከጥንት እንዲህ ዐይነት ከቶ አልነበረም፤ በሚመጡትም ዘመናት እንዲህ ዐይነት ከቶ አይሆንም።
የእግዚአብሔርን ቀን ለምትሹ፣ ለእናንተ ወዮላችሁ! የእግዚአብሔርን ቀን ለምን ትሻላችሁ? ያ ቀን ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም።
ከቀኑ ስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።
ብዙ ቀን፣ ፀሓይንም ከዋክብትንም ማየት ስላልተቻለና ነፋስ ስለ በረታብን፣ ለመትረፍ የነበረን ተስፋ ሁሉ ተሟጠጠ።
ይህች ምድር አምላክህ እግዚአብሔር የሚንከባከባት፣ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ የአምላክህ የእግዚአብሔር ዐይን ምን ጊዜም የማይለያት ናት።
ዐምስተኛውም መልአክ ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውም መንግሥት በጨለማ ተዋጠ፤ ሰዎችም ከሥቃያቸው የተነሣ ምላሳቸውን ያኝኩ ነበር፤