ትካዜ ምግብ ሆኖኛልና፤ የሥቃይ ጩኸቴም እንደ ውሃ ይፈስሳል።
“አሁን ነፍሴ በውስጤ ዐለቀች፤ የመከራ ዘመንም ይዞኛል።
ያኔም ሕይወቱ መብልን ትጠላለች፤ ነፍሱም ምርጥ ምግብን ትጠየፋለች።
እንዲህ ዐይነቱን ምግብ እጸየፋለሁ፤ ለመንካትም አልፈልግም።
ዐይንህን ከእኔ ላይ አታነሣምን? ምራቄን እንኳ እስክውጥ ፋታ አትሰጠኝምን?
ዐመድ እንደ እህል ቅሜአለሁና፤ መጠጤንም ከእንባ ጋራ ቀላቅያለሁ።
ቀኑን ሙሉ ከመቃተቴ የተነሣ፣ ዝም ባልሁ ጊዜ፣ ዐጥንቶቼ ተበላሹ፤
እጅግ ዝያለሁ፤ ፈጽሞም ደቅቄአለሁ፤ ከልቤም መታወክ የተነሣ እጮኻለሁ።
የእንባ እንጀራ አበላሃቸው፤ ስፍር የሞላ እንባም አጠጣሃቸው።
ሁላችን እንደ ድቦች እናላዝናለን፤ እንደ ርግቦችም በመቃተት እንጮኻለን፤ ፍትሕን ፈለግን፤ ግን አላገኘንም፤ ትድግናን ፈለግን፤ ነገር ግን ከእኛ ርቋል።
ርዳታ ፈልጌ ብጣራና ብጮኽ እንኳ፣ ጸሎቴን መስማት አልፈለገም።
እስራኤላውያን በምጽጳ በተሰበሰቡ ጊዜ፣ ውሃ ቀድተው በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሱ፤ በዚያች ዕለት ጾሙ፤ በዚያም “እግዚአብሔርን በድለናል” ብለው ተናዘዙ። ሳሙኤልም በምጽጳ እስራኤልን ይፈርድ ነበር።