ሁሉን ቻይ አምላክ ከእኔ ጋራ ነበረ፤ ልጆቼም በዙሪያዬ ነበሩ፤
እርሱን የት እንደማገኘው ባወቅሁ፤ ወደ መኖሪያውም መሄድ በቻልሁ!
እኔም ብርቱ ነበርሁ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅነት ቤቴን ይባርክ ነበር፤
መንገዴ በቅቤ የራሰ ነበር፤ ዐለቱም የወይራ ዘይት ያመነጭልኝ ነበር።
ሚስትህ በቤትህ፣ እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ ወንዶች ልጆችህ በማእድህ ዙሪያ፣ እንደ ወይራ ተክል ናቸው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ ሞገስ፣ ተራሮቼ ጸኑ፣ ፊትህን በሰወርህ ጊዜ ግን፣ ውስጤ ታወከ።
አምላክ ሆይ፤ አንተ ብርታቴ ነህና፣ ለምን ተውኸኝ? ጠላትስ እያስጨነቀኝ፣ ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?
የልጅ ልጆች ለአረጋውያን ዘውድ ናቸው፤ ወላጆችም ለልጆቻቸው አለኝታ ናቸው።
ወደ ግብዣው አዳራሽ ወሰደኝ፤ በእኔ ላይ ያለው ዐላማው ፍቅር ነው።
አንተ የእስራኤል ተስፋ፤ በጭንቀት ጊዜ አዳኙ፣ ለምን በምድሪቱ እንደ ባዕድ፣ እንደ ሌት ዐዳሪ መንገደኛ ትሆናለህ?
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ሙሽራው ዐብሯቸው እያለ ዕድምተኞቹ እንዴት ሊያዝኑ ይችላሉ? ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያም ጊዜ ይጾማሉ።
በምትሄድበት ሁሉ እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ ጋራ ነውና አይዞህ፤ በርታ፤ ጽና፤ አትፍራ፤ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?”