የመኳንንት ድምፅ ጸጥ ይል፣ ምላሳቸውም ከላንቃቸው ጋራ ይጣበቅ ነበር፤
እኔ ከተናገርሁ በኋላ፣ የሚናገር ሰው አልነበረም፤ ቃሌም እየተንጠባጠበ በጆሯቸው ይገባ ነበር።
ሳላስታውስሽ ብቀር፣ ኢየሩሳሌምን የደስታዬ ቍንጮ ባላደርግ፣ ምላሴ ከትናጋዬ ጋራ ትጣበቅ።
ዐመፀኛ ቤት ቢሆኑም ልትገሥጻቸው እንዳትችል ምላስህን ከላንቃህ ጋራ አጣብቃለሁ፤ ድዳም ትሆናለህ።