ሰው እጁን በቡላድ ድንጋይ ላይ ያነሣል፤ ተራሮችንም ከሥር ይገለብጣል።
በድንጋይ ውስጥ መተላለፊያ ያበጃል፤ ዐይኖቹም የከበሩ ነገሮችን ሁሉ ያያሉ።
ኵሩ አራዊት አልረገጡትም፤ አንበሳም በዚያ አላለፈም።
ሳያውቁት፣ ተራሮችን ይነቅላቸዋል፤ በቍጣውም ይገለብጣቸዋል።