“ታዲያ፣ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች? ማስተዋልስ የት ትገኛለች?
“ነገር ግን ጥበብ ከወዴት ትገኛለች? ማስተዋልስ መኖሪያዋ የት ነው?
ከሕያዋን ፍጥረታት ዐይን ሁሉ ተሰውራለች፤ ከሰማይ ወፎችም ተሸሽጋለች።
ወደ እርሷ የሚወስደውን መንገድ የሚረዳ፣ መኖሪያዋንም የሚያውቅ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤
ከዚያም ሰውን፣ ‘እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው’ አለው።”
እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከአንደበቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣል።
በጎ ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ ከላይ፣ ከሰማይ ብርሃናት አባት ይወርዳሉ፤ በርሱ ዘንድ መለዋወጥ፣ ከመዞር የተነሣ የሚያርፍ ጥላም የለም።
ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጐድለው፣ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉም የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለርሱም ይሰጠዋል።