ብረት ከመሬት ውስጥ ይገኛል፤ መዳብም ከማዕድን ድንጋይ ቀልጦ ይወጣል።
ሴላም ደግሞ ቱባልቃይን የተባለ ወንድ ልጅ ነበራት፤ እርሱም ከብረትና ከናስ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እየቀረጸ የሚሠራ ነበር። የቱባልቃይን እኅት ናዕማ ትባል ነበር።
“ለእግዚአብሔር ቤት እንዲሆንም አንድ ሺሕ መክሊት ወርቅ፣ አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፣ ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይቻል ናስና ብረት ለማዘጋጀት በተቻለኝ ሁሉ ጥሬአለሁ፤ በተረፈ አንተ ጨምርበት።
“የብር ማዕድን የሚወጣበት፣ ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ።
ሰው፣ እስከ ጨለማ መጨረሻ ይዘልቃል፤ ከድቅድቅ ጨለማ የማዕድን ድንጋይ ለማግኘት፣ እስከ ውስጠኛው ዋሻ ገብቶ ይፈልጋል።
ወርቅ፣ ብር፣ ናስ፣ ብረት፣ ቈርቈሮ፣ እርሳስ
ምንም ነገር የማይታጣባት፣ የዳቦም ዕጦት የሌለባት፣ ዐለቶች ብረት የሆኑባት፣ ከኰረብቶቿም መዳብ ቈፍረህ ልታወጣ የምትችልባት ምድር ናት።