ንጹሕ ወርቅ ሊገዛት አይችልም፤ ዋጋዋም በብር አይመዘንም።
ውቅያኖስ፣ ‘በእኔ ውስጥ የለችም’ ይላል፤ ባሕርም፣ ‘በእኔ ዘንድ አይደለችም’ ይላል።
በኦፊር ወርቅ፣ በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም።
ዛጐልና አልማዝ ከቍጥር አይገቡም፤ የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍም ይበልጣል።
ከወርቅ ይልቅ ጥበብን ማግኘት፣ ከብርም ማስተዋልን መምረጥ ምንኛ ይበልጣል!
የሚወድዱኝን እወድዳቸዋለሁ፤ ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል።
ፍሬዬ ከንጹሕ ወርቅ ይበልጣል፤ ስጦታዬም ከነጠረ ብር።