“ጠላቴ እንደ በደለኛ፣ ባላንጣዬም እንደ ክፉ ይሁን።
ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን፣ “ብላቴናው አቤሴሎም ደኅና ነውን?” ሲል ጠየቀው። ኢትዮጵያዊውም፣ “የጌታዬ የንጉሡ ጠላቶችና ሊጐዱህ የሚነሡብህ ሁሉ እንደዚያ ወጣት ይሁኑ” ሲል መለሰ።
ጽድቄን አጥብቄ እይዛለሁ፤ አልለቀውምም፤ በዘመኔም ሁሉ ኅሊናዬ አይወቅሠኝም።
እግዚአብሔር ሲያስወግደው፣ ነፍሱንም ሲወስድበት ዐመፀኛ ምን ተስፋ አለው?
“ምነው የሚሰማኝ ባገኝ! የመከላከያ ፊርማዬ እነሆ፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ይመልስልኝ፤ ከሳሼም ክሱን በጽሑፍ ያቅርብ።
ከዚያም ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል ለጥቂት ጊዜ በጣም ታወከ፤ ሐሳቡም አስደነገጠው። ንጉሡም፣ “ብልጣሶር ሆይ፤ ሕልሙም ሆነ ትርጕሙ አያስደንግጥህ” አለው። ብልጣሶርም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “ሕልሙ ለሚጠሉህ ይሁን፤ ትርጕሙም ለጠላቶችህ!
ጌታዬ ሆይ፤ ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ ደም ከማፍሰስና በገዛ እጅህ ከመበቀል የጠበቀህ እግዚአብሔር ነው፤ አሁንም ጠላቶችህና ጌታዬን ሊጐዱ የሚፈልጉ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ፤