ከንፈሬ ኀጢአትን አትናገርም፤ አንደበቴም ሽንገላ አይወጣውም።
ለእግዚአብሔር ብላችሁ በክፋት ትናገራላችሁን? ስለ እርሱስ በማታለል ታወራላችሁን?
ነገር ግን በእጄ ዐመፅ አይገኝም፤ ጸሎቴም ንጹሕ ነው።
“ይህ እንዲህ ካልሆነማ፣ የሚያስተባብለኝ ማን ነው? ቃሌን ከንቱ የሚያደርገውስ ማን ነው?”
ቃሌ ከቅን ልብ ይወጣል፤ ከንፈሬም የማውቀውን በትክክል ይናገራል።
እውነተኛ ብሆንም፣ እንደ ውሸታም ተቈጥሬአለሁ፤ በደል ባይኖርብኝም፣ በማይፈወስ ቍስል ተመትቻለሁ።’
“አሁን ግን ፈቃዳችሁ ቢሆን ወደ እኔ ተመልከቱ፤ ፊት ለፊት እዋሻችኋለሁን?
እናንተ ባታውቁትም እኔ ዐውቀዋለሁ፤ አላውቀውም ብል፣ እኔም እንደ እናንተው ሐሰተኛ እሆናለሁ። እኔ ግን ዐውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ።
የክርስቶስ እውነት በውስጤ እስካለ ድረስ፣ በአካይያ አውራጃ ይህን ትምክሕቴን ማንም ሊገታው አይችልም።