እርሱ ያከማቸውን ጻድቃን ይለብሱታል፤ ብሩንም ንጹሓን ይከፋፈሉታል።
በዚያ ዕለት ንጉሥ ጠረክሲስ የአይሁድን ጠላት የሐማን ቤት ንብረት ለንግሥት አስቴር ሰጣት፤ አስቴርም መርዶክዮስ እንዴት እንደሚዛመዳት ለንጉሡ ነግራው ስለ ነበር፣ መርዶክዮስ ወደ ንጉሡ ዘንድ ቀረበ።
ከእንግዲህ ባለጠጋ አይሆንም፤ ሀብቱም አይቈይም፤ ይዞታውም በምድር ላይ አይሰፋም።
ልጆቹ ለድኾች ካሳ መክፈል አለባቸው፤ እጆቹም ሀብቱን መልሰው መስጠት ይገባቸዋል።
የለፋበትን ሳይበላው ይመልሳል፤ ከንግዱም ባገኘው ትርፍ አይደሰትም፤
ብርን እንደ ዐፈር ቢከምር፣ ልብስንም እንደ ሸክላ ጭቃ ቢያከማች፣
ቤታቸውን በብር ከሞሉ፣ ወርቅም ከነበራቸው ገዦች ጋራ ባረፍሁ ነበር።
ደግ ሰው ለልጅ ልጆቹ ውርስ ትቶ ያልፋል፤ የኀጢአተኞች ሀብት ግን ለጻድቃን ይከማቻል።
በከፍተኛ ወለድ ሀብቱን የሚያካብት፣ ለድኻ ለሚራራ፣ ለሌላው ሰው ያከማችለታል።
አምላክ፣ ደስ ለሚያሠኘው ሰው ጥበብን፣ ዕውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል። ለኀጢአተኛ ግን፣ አምላክን ደስ ለሚያሠኘው ይተውለት ዘንድ፣ ሀብትን የመሰብሰብና የማከናወን ተግባር ይሰጠዋል። ይህም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
እናንተ በመክቴሽ ገበያ የምትኖሩ ዋይ በሉ፤ ነጋዴዎቻችሁ ሁሉ ይደመሰሳሉ፤ በብር የሚነግዱትም ሁሉ ይሞታሉ።