“እግዚአብሔር ለክፉው ሰው የመደበው ዕድል ፈንታ፣ ግፈኛም ሁሉን ቻይ አምላክ የሚቀበለው ቅርስ ይህ ነው፦
ሁላችሁ ይህን አይታችኋል፤ ታዲያ፣ ይህ ከንቱ ንግግር ምንድን ነው?
ከላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሰው ዕድል ፈንታው፣ ከአርያም ከሁሉን ቻይ አምላክስ ዘንድ ቅርሱ ምንድን ነው?
ለኀጢአተኞች ጥፋት፣ ክፉ ለሚያደርጉም መቅሠፍት አይደለምን?
እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤ የጽዋቸውም ዕጣ ፈንታ፣ የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስ ነው።
እግዚአብሔር፣ “ስለ ችግረኞች መከራ፣ ስለ ድኾችም ጩኸት፣ አሁን እነሣለሁ፤ በናፈቁትም ሰላም አኖራቸዋለሁ” ይላል።
ነገር ግን ክፉዎች አምላክን ስለማይፈሩ መልካም አይሆንላቸውም፤ ዕድሜያቸው እንደ ጥላ አይረዝምም።
በደለኞች ወዮላቸው! ጥፋት ይመጣባቸዋል! የእጃቸውን ያገኛሉና።
“ስለዚህ እኔ ለፍርድ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በመተተኞች፣ በአመንዝራዎች፣ በሐሰት በሚምሉ፣ የሠራተኞችን ደመወዝ በሚከለክሉ፣ መበለቶችንና ድኻ አደጉን በሚጨቍኑ፣ መጻተኞችን ፍትሕ በሚነፍጉ፣ እኔንም በማይፈሩት ላይ እመሰክርባቸው ዘንድ እፈጥናለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ጌታ፣ በእውነት እያመለኩት የሚኖሩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸውና ዐመፀኞችን እየቀጣ ለፍርድ ቀን እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።